Posts

                     አንቀፅ-17 ነፃነት/ባርነት * ከአድዋ-ጎሎጎታ ይህ ታሪክ ከተፈፀመ እነሆ በዛሬዉ 122 ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ ይህ ቀን ለአሁኗ ኢትዮጲያ ማንነቷን ያስጠበቀችበት ከባርነት ራስዋን ነፃ ያደረ ገችበት ቀን ነዉ፡፡ ከመላዉ የአለም ሃያላን የተነሳን ከባድ የባርነት በትር በፅኑ ትግል ከጫንቃዋ ያነሳች ብሎም ለመላዉ የአፍሪካ ሀገራትና ህዝቦች የነፃነት ምክንያት ነበረች፡፡ እስቲ ከምክንያት ጋር ለማየት እንዲረዳን የዚህን ታሪካዊ ስፍራ ስያሜና ለዚህ ታሪካዊ ጦርነት መነሻ የነበረዉን ነገር እናንሳ፡፡ የአድዋ የስሙን ትርጓሜ ከ ጣሊያናዊዉ ኢትዮጲያን ወዳድ ሪቻርድ ፓንክረስት ከተፃፈዉ ፅሁፍ ብንመለከት አድዋ ማለት (village of the awa) ማለትም “የአዋዎች መኖሪያ” ማለት ሲሆን ይህ ስፍራ ለ ንግድ ስራ ለረጅም ጊዜያት ምቹ ስፍራ ሆኖም አገልግሏል:: ብሎም ለነገስታት ዋና መቀመጫቸዉና ከተለያዩ የአለም ክፍላት የሚመጡ ሰዎችን መቀበያ ሰፍራቸዉም ሆና አገልግላለች ፡፡ለነዚህ ሁሉ ነገር ተፈላጊ ያደረጋት ምክንያትም ያላት መልካምድራዊ አቀማመጥ ለዚህ ሁሉ ነገር ምቹ ስፍራ አድርጓት ቆይቷል፡፡እንዲሁም ትልቁ የመገባቢያ ስፍራም ነበረች በ 1890እ.ኤ.አ በ አዉግስጦስ ቢ.ዌይልድ የአድዋን የገበያ ስፍራ ከተመለከተ በኃላ “ሁሉንም የምርት አይነቶችን ፈልጎ ማይታጣባት” ሲል ገልፆታል፡፡በቴክኖሎጂዉም ዘርፍ ቢሆን ከ አስመራ-አዲስ አበባ የተዘረጋዉ የቴሌግራፍ መስመር ያለፈባት ሲሆን በዚህም ምክንያት ቢሮዉን በዛ ስፍራም ለመክፈት ተችሏል፡፡ ብሎም የቴሌግራፍ አገልግሎት ለትግራይ ክልል ያስገየችም ነበረች፡፡እናም በዚህ ስፍራ ይደረጉ ለነበሩ የልማት ዝርጋታዎች የጣሊያን መንግስት የተለያዩ ስራዎችን በዚሁ አካባቢ ላይ ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር